Trainers training on common courses

October 26, 2026 | By genet
Trainers training on common courses

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስተባባሪነት የሚሰጠው የኮመን ኮርሶች የአሰልጣኞች ስልጠና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ


በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አሰልጣኞች የተዘጋጀው የኮመን (Common) ኮርሶች የአሰልጣኞች ስልጠና በዛሬው ዕለት ጥቅምት 15 ቀን 2019 ዓ.ም. በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በይፋ ተጀምሯል።

በስልጠናው የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፅሐይ ቦጋለ ስልጠናውን በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን፣ የአሰልጣኞች አቅም ግንባታ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትን ጥራት ለማሻሻል የሚኖረውን ከፍተኛ ሚና አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።


ስልጠናው በቴክኒክና ሙያ ትምህርት የሚሰጡ ሦስቱን የጋራ (Common) ኮርሶች ማለትም ኢንተርፕሪነርሺፕ (Entrepreneurship)፣ Human Edge እና ሲቪክስና ሥነ-ምግባር (Civics and Ethics) ለሚያስተምሩ የተመረጡ አሰልጣኞች የተዘጋጀ ሲሆን፣ ለ10 ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል።

የስልጠናው ዋና ዓላማ የአሰልጣኞችን የሙያ ብቃት፣ የማስተማር ክህሎት እና የዘመናዊ የማስተማር ስልቶችን በማጠናከር የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ጥራትን ማሻሻል ነው። በስልጠናው የሚሳተፉ አሰልጣኞች በሚያገኙት እውቀትና ክህሎት በየተቋማቸው የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ ይጠበቃል።

Share this article

Related Articles

Life skills
Life skills
Nov 4, 2026
Welcome
Welcome
Nov 4, 2026
Entrepreneurship Training
Entrepreneurship Training
Nov 4, 2026