Life skills

November 4, 2026 | By genet
Life skills

ብቃት» የወጣቶች የሕይወት ክህሎት እና የሥራ ማፈላለግ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ተጠናቀቀ።


ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም /DMPTC/


የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት መምሪያ ጋር በቅንጅት ለ12 ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የቆየው «ብቃት» የወጣቶች የሕይወት ክህሎት እና የሥራ ማፈላለግ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በዛሬው ዕለት ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።


ስልጠናው ወጣቶች የሕይወት ክህሎታቸውን እንዲያጎለብቱ፣ የሥራ ገበያውን በተገቢው ሁኔታ እንዲረዱ፣ የሥራ ፍለጋ ሂደቶችን በብቃት እንዲያከናውኑ እንዲሁም ለቀጣሪዎች ተፈላጊ የሆኑ የሙያና የስነ-ባህሪ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ ያተኮረ ነበር። በስልጠናው ውስጥ የቃለ መጠይቅ ዝግጅት፣ የመግባቢያ ክህሎት፣ የቡድን ሥራ፣ የችግር ፈቺነት፣ የሥራ ሥነ-ምግባር፣ የራስ መተማመን እና ሌሎች ለቅጥር እና ለሥራ ስኬት ወሳኝ የሆኑ ክህሎቶች ተሰጥተዋል።


በስልጠናው የማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ልምድ በመግለጽ ለአሰልጣኞ የምስጋና እና የእውቅና መልዕክቶችን አቅርበዋል፤ ስልጠናው በሕይወታቸው እና በሥራ ፍለጋ ዝግጅታቸው ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንዳሳደረባቸውም ገልጸዋል።


በመጨረሻም ይህ ስልጠና በተሳካ እና ውጤታማ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ላስተባበሩ፣ ላሰለጠኑ፣ ድጋፍ ላደረጉ አካላት እና በትጋት ለተሳተፉ ሰልጣኞች በሙሉ ከልብ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

Share this article

Related Articles

Welcome
Welcome
Nov 4, 2026
Entrepreneurship Training
Entrepreneurship Training
Nov 4, 2026
In company training
In company training
Oct 29, 2026