በደብረ ማርቆስ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከተለያዩ የአረብ ሀገራት ለተመለሱ ዜጎች የሥራ ፈጠራ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ
ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም. (DMPTC)
በደብረ ማርቆስ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከተለያዩ የአረብ ሀገራት ተመልሰው ለመጡ ዜጎች የኢኮኖሚ አቅምን ለማጎልበትና በራሳቸው ሥራ ተሰማርተው ዘላቂ የኑሮ መሠረት እንዲፈጥሩ የሚያግዝ የሥራ ፈጠራ ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል።
ስልጠናው በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት መምሪያ እና በደብረ ማርቆስ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የጋራ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ በከተማው የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋፋት፣ ተመላሽ ዜጎችን በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ የታለመ መርሃ ግብር ነው።
በስልጠናው ወቅት ተሳታፊዎች በሥራ ፈጠራ፣ በአነስተኛና ጥቃቅን ንግድ ሥራ አጀማመር፣ በቢዝነስ እቅድ ዝግጅት፣ በፋይናንስ አስተዳደር፣ በገበያ ትስስር እና በራስ ሥራ ፈጠራ ዙሪያ ተግባራዊ እውቀትና ክህሎት የሚያገኙ ይሆናል።
ደብረ ማርቆስ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሀገሪቱን የክህሎት ልማት ፖሊሲ በመደገፍ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በገበያ ተኮር ስልጠናዎች በማብቃት የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋፋት የሚያደርገውን ጥረት በቀጣይነት ያጠናክራል።