Recognition certificate

October 22, 2026 | By genet
Recognition certificate

🏅 ለደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከአማራ ልማት ማህበር የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጠ!


⏩ ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት ከአማራ ልማት ማህበር ጋር በመተባበር ላከናወናቸው የበጎ ፈቃድና የማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎች ከፍተኛ እውቅና አግኝቷል።


በዚሁ መሰረት ኮሌጁ ከአማራ ልማት ማህበር የምስጋና ምስክር ወረቀት እና ሜዳሊያ በመቀበል ለማህበረሰብ አገልግሎትና ለበጎ ፈቃድ ተግባራት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል።

ይህ እውቅና ኮሌጁ ከመደበኛ የትምህርትና ስልጠና ተግባራቱ ባሻገር ለማህበረሰቡ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ እና ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር የሚያከናውነውን የልማት ተግባር የሚያሳይ ነው።

ኮሌጃችን ወደፊትም በማህበራዊ ኃላፊነት ሥራዎች፣ በበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴዎች እና በማህበረሰብ ልማት ተግባራት ያለውን ተሳትፎ በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል።


ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም

ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


"በጥራት ትምህርት፣ በክህሎት ልማት፣ ለማህበረሰብ ተጠያቂነት!"

Share this article

Related Articles

Life skills
Life skills
Nov 4, 2026
Welcome
Welcome
Nov 4, 2026
Entrepreneurship Training
Entrepreneurship Training
Nov 4, 2026