Poultry Cage

October 16, 2026 | By admin
Poultry Cage

የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንኩቤሽን ማዕከል ምስለ ምርቶች (Prototypes) ቴክኖሎጂዎችን ወደ ምርት አሸጋገረ።

✅ የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንኩቤሽን ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት በኮሌጁ የተፈጠሩ ምስለ ምርቶች (Prototypes) ቴክኖሎጂዎችን ከሙከራ ደረጃ ወደ ሰፊ ምርት (Mass Production) የማሸጋገር ሥራ በይፋ ጀምሯል።

ወደ ምርት የተሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎች በዘርፉ ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በይፋ የተላለፉ ሲሆን፣ በቀጣይ የሚመረቱ ተጨማሪ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ለማምረት ከኢንተርፕራይዞች ጋር የትብብርና የምርት ውል ስምምነት ተፈራርሟል።

✅ኮሌጁ በምርምር፣ በፈጠራ እና በቴክኖሎጂ ልማት የሚፈጠሩ ፈጠራዎችን ወደ ተግባራዊ ምርት በመቀየር ለኢንዱስትሪ እድገት፣ ለሥራ ፈጠራ፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና ለአካባቢው ኢኮኖሚ እድገት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

⏩ በቀጣይም በኮሌጁ የሚፈጠሩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ምርት በማሸጋገር ለኢንተርፕራይዞች፣ ለኢንዱስትሪዎች እና ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የምርት ሂደቱ በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ጥቅምት 6/2019 ዓ.ም.

ደብረ ማርቆስ

Share this article

Related Articles

Life skills
Life skills
Nov 4, 2026
Welcome
Welcome
Nov 4, 2026
Entrepreneurship Training
Entrepreneurship Training
Nov 4, 2026