career and technical education

October 26, 2026 | By genet
career and technical education

በደብረ ማርቆስ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና በደብረ ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ መካከል የሙያና ቴክኒክ ትምህርት (Career and Technical Education) ዕጩ መምህራንን በትብብር ለማሰልጠን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ


ጥቅምት 14/2019 ዓ.ም – ደብረ ማርቆስ

በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የሚተገበረውን የሙያና ቴክኒክ ትምህርት (Career and Technical Education) ፕሮግራም ውጤታማ ለማድረግ በሙያ የሰለጠኑ መምህራንን ማፍራት ወሳኝ በመሆኑ፣ በደብረ ማርቆስ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና በደብረ ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ መካከል ዕጩ መምህራንን በጋራ ለማሰልጠን የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል።

የስምምነቱ ዋና ዓላማ ለመካከለኛ ደረጃ የሙያና ቴክኒክ ትምህርት (Career and Technical Education) ፕሮግራም የሚዘጋጁ ዕጩ መምህራን የሚወስዷቸውን የሙያ ኮርሶች በሁለቱ ተቋማት በትብብር በመስጠት የተግባር ክህሎታቸውን ማጎልበትና ብቁ የሙያ መምህራንን ማፍራት ነው።

በዚሁ መሠረት በዛሬው ዕለት ጥቅምት 14/2019 ዓ.ም. በስምምነቱ ላይ ከሚመለከታቸው ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት ከተካሄደ በኋላ በሁለቱ ተቋማት ዲኖች የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

ይህ የትብብር ስምምነት በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን አካዳሚያዊ ትብብር ከማጠናከሩ ባሻገር፣ በሀገራችን የሙያና ቴክኒክ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል፣ ብቁ እና በተግባር የተካኑ መምህራንን ለማፍራት እንዲሁም የተቋማት ትብብርን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

Share this article

Related Articles

Life skills
Life skills
Nov 4, 2026
Welcome
Welcome
Nov 4, 2026
Entrepreneurship Training
Entrepreneurship Training
Nov 4, 2026