🖼 እንኳን ደስ አለን!እንኳን ደስ አላችሁ!

# ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዓለም አቀፍ የትምህርት ተቋም አስተዳደር ሥርዓት ISO 21001:2025 (EOMS) በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ በማድረጉ certified ሆነ።
ኮሌጁ ባሳለፍነው አንድ አመት በISO 21001:2025 ብቁ ለመሆን የሰነድ ዝግጅት እና የመሠረተ ልማት ስራዎችን በእስታንዳርዱ መሰረት ሲተገብር ቆይቶ በኢትዩጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በኦዲት ተረጋግጦ መስፈርቱን ሥላሟላ ለዚህ ታሪካዊ ዉጤት በቅቷል።
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ ለኮሌጁ ዲን አቶ አስጨነቅ ካሳ ሰርቲፊኬቱን አስረክበዋል፡፡
በርክክብ ስነ- ስርዓቱ ላይ ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ኮሌጁ በISO 21001:2025/EOMS/ ብቁ መሆኑ የኮሌጁን የስልጠና አሰጣጥ ማዘመን እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እዲያስችል ትልቅ ዕድልን ይፈጥራል። እንዲሁም ኮሌጁ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ÷ በቴክኖሎጅ እና በክህሎት ልማት የልህቀት ማዕከል ይሆናል።
ለኮሌጃችን ሰራተኞች፣ ሠልጣኞች ÷ በቅርብ ክትትል እና ድጋፋ ለአደረጋችሁልን ለቢሯችን ለአብክመ ሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች ÷የኮሌጁ ቦርድ አባላት እና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፎ ላደረጋችሁ ለደብረ ማርቆሥ እና አካባቢው ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን።
ሰኔ 29/2018 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ
Building Competence, Driving Innovation!