Industry TVET Linkage

August 11, 2026 | By admin
Industry TVET Linkage

በደብረ ማርቆስ ከተማ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አስተባባሪ ፎረም ተመሠረተ::


ነሐሴ 3/2018 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት መምሪያ እና በደብረ ማርቆስ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በትብብር፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አስተባባሪ ፎረም ምስረታ፣ በ2018 ዓ.ም ለኮሌጁ የትብብር ስልጠና የሰጡ እና ለምሩቃን የሥራ ትስስር የፈጠሩ ኢንዱስትሪዎች የምስጋናና የእውቅና ፕሮግራም፣ እንዲሁም የTracer Study እና Industry Needs Assessment ጥናቶች ውጤቶች የቀረቡበት ወርክሾፕ ተካሂዷል።

ፕሮግራሙን በክብር እንግድነት ተገኝተው በይፋ ያስጀመሩት የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ እና የኮሌጅ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተሾመ ዋለ ሲሆኑ፣ በንግግራቸው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለአገር ልማት መሠረታዊ አቅም መሆኑን ገልጸው፣ በኮሌጁና በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለው ትብብር በተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል። እንዲሁም የትብብር ስልጠና ሰልጣኞችን በሥራ ዓለም ተወዳዳሪ ለማድረግና የተቋማትን ምርታማነት ለማሳደግ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ መኮነን ሙሉአዳም በበኩላቸው፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር የመግባቢያ ሰነዶች (MoU) በመፈራረም ዘላቂ የትብብር ማዕቀፍ በመፍጠር ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራትና ለምሩቃን የሥራ ዕድል ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በወርክሾፑ የTracer Study እና Industry Needs Assessment ጥናቶች ውጤቶች በኮሌጁ ኢንስትራክተር ዶ/ር ዋለ ፍሬው ቀርበው በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በመድረኩ የትኩረት መንግሥት መሥሪያ ቤት ሀላፊዎች ፣ ኢንዱስትሪ ባለቤቶችናባለድርሻ አካላት በሰፊው ተሳትፈዋል።


ነሐሴ 3 /2018 ዓ.ም

ደብረ ማርቆስ


Share this article

Related Articles

cur
cur
Sep 4, 2026
Registrar
Registrar
Sep 4, 2026
Registration
Registration
Aug 24, 2026