የደብረ ማርቆስ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በክረምት በጎ ፈቃድ የተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑን ተገለፀ።
****
የደብረ ማርቆሥ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሚሠራቸው መደበኛ ተግባር በተጨማር በክረምት በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት እየሠጠ ሲሆን በዛሬው እለትም የተለያዩ ግባቶችን እርክክብ አድርጎል።
ኮሌጁ ለ2019 የትምህርት ዘመን የመማሪያ ቁሳቁሥ ለሚቸገሩ ለ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች አገልግሎት የሚውል
50 ደርዘን ደብተር፣
10 ፓኮ እስክርቢቶ፣
እና ለተማሪ ዩኒፎርም እና አልባሳት ድጋፋ ለሚያሥፈልጋቸው አገልግሎት የሚውል የተለያየ አልባሳት ብዛት 404 ድጋፋ የተደረገ ሲሆን የክረምት ማህበረሰብ አገልግሎት ሥራው ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም
ደብረ ማርቆሥ