በደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ21ኛዉ ክፍለ ዘመን /Soft skill/የሂወት ክህሎት እና ሊደርሸፕ ስልጠና ተሰጠ።
===================
ደብረ ማርቆስ ግንቦት 29/2018ዓ.ም
የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለሴት የስራ ሂደት አስተባባሪዎች፣ የዘርፍ ተጠሪዎች እንዲሁም ከክላስተር ኮሌጅ ለመጡ የስርአተ ጾታ ተወካይ የሶፍት ስኪል ስልጠና ተሰጥቷል።
በኮሌጁ የኢዝ ፕሮጀክት/EASE Project/አዘጋጅነት የተሰጠው ይህ ስልጠና አላማ ሴት ሰራተኞች በራሳቸው ሀላፊነት ወስደው ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ እና ወደ ከፍተኛ ሀላፊነት እንዲመጡ ፣ችግር ፈች በመሆን በትብብር የመስራት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ማድረግ ነዉ። ሰልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ በመጡ የዘርፋ መምህር የተሰጠ ነዉ።