Bichena TVET College Experience Sharing

August 16, 2026 | By admin
Bichena TVET College Experience Sharing

የብቸና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ልዑካን ቡድን በደብረ ማርቆስ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡

#DMPTC ነሐሴ 7/ 2018 ደብረ ማርቆስ


የብቸና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲኖችን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በኮሌጃችን ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት እንዲሁም ያለውን ተሞክሮ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን የስራ ልምድ ልውውጥ በኮልጁ አካሂደዋል::


ልዑካን ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብር ወቅትም የደብረ ማረቆስ ፖሊቴክኒክ በተቋም ደረጃ እየሰራቸዉ ያሉ ስራዎችን በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ በተደረገላቸው አቀባበልና በተመለከቱት የኮሌጁ እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ የደብረ ማርቆስ ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች በጣም ጥሩ መሆናቸውን ገልፀው በዚህም ኮሌጁ ከጀመረዉ ውጤታማ ጉዞ ብዙ ልምዶችን መቅሰም መቻላቸውንም ገልፀዋል::


በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የስልጠና ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በነበራቸው የልምምድ ልውውጥ መርሃ-ግብርም የተሳካ ቆይታን በኮሌጃችን ማድረግ ችለዋል::


ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-

በቴሌግራም፡- https://telegram.me/dmtvet1990

በፌስቡክ ፔጃችንን ፡-https://m.facebook.com/Debre-Markos-Poly-Technic-College-

በድረ ገጽ ፡ www.https://dmptc.edu.et/

Share this article

Related Articles

cur
cur
Sep 4, 2026
Registrar
Registrar
Sep 4, 2026
Registration
Registration
Aug 24, 2026