DMPTC EASE project

March 20, 2026 | By admin
DMPTC EASE project

በአይሶ(ISO) አተገባበርና የኢዝ ፕሮጀክት አፈፃፀም ወርክሾፕ

በ2018 በጀት ዓመትም የተመረጡ ፓሊ ቴክኒክ  ኮሌጆች አይሶን ተግባራዊ ለማድረግ የጀመሩትን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ቢሮው የበኩሉን ጥረት በማድረግ ላይ ያለ ሲሆን የደብ ማርቆሥ  ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አይሶን(ISO) በዚህ ዓመት ከሚተገብሩ ኮሌጆች መካከል አንዱ ነው።

የደብረ ማርቆሥ  ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የአይሶ(ISO) 21001:2025 የደረሰንበትን አፈፃፀም እና እየተተገበሩ ያሉ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎች በአስተባባሪው/MR/ አቶ ግርማ  ገዳሙ   አማካኝነት ሪፖርቱ ቀርቧል።

በውይይት ወርክሾፑ የኢፌዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ የተከበሩ ዶክተር ተሻለ በሬቻ÷ የአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ስቡህ ገበያው እና የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አማረ ዓለሙ እና ሌሎች የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የኢዝ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆችና አይሶን በመተግበር ላይ የሚገኙ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ዋና ዲኖች ተገኝተዋል።

በሌላ በኩል በስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ከአለም ባንክ ኢዝ ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ በክልሉ ተጠቃሚ የሆኑት ሶስት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የ2018 በጀት ዓመት የፕሮጀክቱ የሰባት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል።

የደብረ ማርቆሥ  ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅም የኢዝ ፕሮጀክት የሰባት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱን የደብረ ማርቆሥ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኢዝ ፕሮጀክት አስተባባሪው አቶ ደሴ አያሌው ለተሳታፊዎች አቅርበዋል።

አዲስ አበባ: መጋቢት 04/2018 ዓ.ም

Share this article

Related Articles

Technology Incubation Center
Technology Incubation Center
Mar 26, 2026
ከመግቢያው በስተግራ በኩል አጥር
ከመግቢያው በስተግራ በኩል አጥር
Mar 20, 2026
ከመግቢያ በር በስተቀኝ በኩል አጥር
ከመግቢያ በር በስተቀኝ በኩል አጥር
Mar 20, 2026